mesmer logo

የ መስመር ፕሮግራም አገልግሎቶችን ለማስጀመር እና ለመጠቀም የሚያገለግሉ ደንቦች እና ሁኔታዎች፡

 1. የውል ስምምነቶች
  1. ይህ ስምምነት ለመስመር አገልግሎቶች ተፈጻሚ የሚሆኑ ሁሉንም ደንቦች እና ሁኔታዎች (ከዚህ በኋላ "እነዚህ ደንቦች እና ሁኔታዎች" የሚባል) ያዘጋጃል።
  2. እነዚህ ደንቦች እና ሁኔታዎች እንዲሁም ከዚህ ጋር የተያያዙ ማሻሻያዎች እና ለውጦች በጸደቁበት ቀን ተፈጻሚ ይሆናሉ።
  3. እርስዎ በህጋዊ አስገዳጅ ስምምነት ውስጥ ለመግባት ተወዳዳሪ እና ብቁ መሆንዎን እና ሌላውን አካል ከዚህ ስምምነት ጋር ለማያያዝ አስፈላጊው ስልጣን እንዳለዎት ይወክላሉ እና ዋስትና ይሰጣሉ። በሚመለከታቸው ህጎች፣ህጎች እና ደንቦች መሰረት ውል ለመስራት ብቁ ካልሆኑ ይህን ፕሮግራም መጠቀም የለብዎትም።
 2. ትርጓሜዎች
  2.1) በእነዚህ ደንቦች እና ሁኔታዎች፤ የሚከተሉት ቃላት እና አባባሎች ከዚህ በታችየተዘረዘሩትን ትርጓሜዎች ይይዛሉ
  የንግድ ስራ ክህሎት አገልግሎት ማለት የንግድ እንቅስቃሴ ለማጎልበት፣ ንግድን ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ እና የገበያ ተደራሽነትንና አቅምን ለማሳደግ የሚያግዝ አገልግሎት፤
  ብድር ማለት በ አበዳሪ ተቋማት(የገንዘብ ተቋማት) እና በተበዳሪዎች (በንግድ ድርጅቶች) መካከል የሚደረግ ከወለድ ጋ ተመልሶ የሚከፈልበት ውል(ስምምነት)፤
  የመጨረሻ ክፍያ ቀን፡ ማለት የ ብድር መመልሻ የጊዜ ገደብ (ገባሪ የ ብድር ጊዜ) ያላለፈ መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን ብርድ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ 30 ቀናትን የሚያካትት ነው።
  ድርጅቶች፡ ማለት በህጋዊ ሁኔታ እና በሰራተኞች ብዛት እና በጠቅላላ ንብረቶች ተለይቶ የሚታወቅ ንግድ ነው። ለዚህ PIM ዓላማ እና ከኢትዮጵያ ሁኔታ ጋር የተጣጣመ፣ ኢንተርፕራይዞቹ የተከፋፈሉ ናቸው። የተከፋፈሉትምየሚከተሉት ናቸው፡

ኢመደበኛ ድርጅቶች ለድጋፍ ብቻ (ብድርን አያጠቃልልም)፡ ምንም አይነት ህጋዊ ምዝገባ ያላከናወኑ ድርጅቶች ናቸው።በአሰራራቸው እና ባላቸው የንብረት መጠን ከ ጥቃቅን ድርጅቶች ጋር ይመሳሰላሉ። ንግዶቹ በአብዛኛው በቤት ውስጥ የሚሰሩ (የንግድ ቦታቸው መኖሪያ ቤታቸው የሆኑ) እና ተንቀሻቃሽ የሆኑ ሲሆኑ የንግዶቹ ቋሚ የሆነ የንግድ ቦታ ችግር ይታይባቸዋል። አነስተኛ የከተማ ግብርናዎች በአብዛኛው ኢመደበኛ ናቸው ነገር ግን የሚፈጥሩት የሚይዙት የሰራተኛ መጠን እና በ በእሴት ሰንሰለት (value chain) እና በጠቅላላ ንብረት አኳያ የተፈጠሩዋቸው ስራዎች ከ መደበኛ ጥቃቅን ንግዶች ጋር ተመሳሳይ ናቸው።

ጀማሪ ድርጅቶች፡ አዲስ የተቋቋመ ንግድ ፍቃድ እና የቲን ቁጥር ያለው። እነዚህ የንግድ ፈቃዳቸውን ካገኙ ከ0-1 ዓመት ሥራ ላይ ያሉ የንግድ ድርጅቶች ናቸው።

ጥቃቅን ድርጅቶች፡ በህጋዊ መንገድ የተመዘገቡ ድርጅቶች፣ እስከ 10 ግለሰቦችን የቀጠሩ እና በአጠቃላይ ከ400,000 እና 600,000 ብር ወይም ከዛ በታች የሆነ የሃብት መጠን ያላቸው፤ ለእርሻ፣ ለአገልግሎት እና ለኢንዱስትሪ ዘርፍ እንደየቅደም ተከተላቸው።

አነስተኛ ድርጅቶች፡- በህጋዊ መንገድ የተመዘገቡ ኢንተርፕራይዞች ከ11 እስከ 30 ግለሰቦችን የቀጠሩ እና በአጠቃላይ ሃብት ከ600,001 እስከ 10,000,000 ብር ለኢንዱስትሪው ዘርፍ ያላቸው እና ከ400,001 እስከ 5,000,000 ብር ለግብርና እና አገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶች።

**መካከለኛ ድርጅቶች፡**በህጋዊ መንገድ የተመዘገቡ ኢንተርፕራይዞች ከ31 እስከ 100 ግለሰቦችን የቀጠሩ እና በአጠቃላይ የሃብት መጠን ከ10,000,001 እስከ 90,000,000 ብር ለኢንዱስትሪው ዘርፍ እና ከ5,000,001 እስከ 50,000,000 ብር በአገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ የንግድ ድርጅቶች ።

የገንዘብ ተቋማት: ባንኮች እና የብድር እና ቁጠባ ተቋማት (ማይክሮ ፋይናንስ)።

እርዳታ፡ የማይመልስ በአንድ ወገን ብቻ የሚሰጥ የገንዘብ ድጋፍ ነው (ለዚህ ፕሮግራም ማስተርካርድ ፋውንዴሽን)

መስመር ፕሮግራም፡ ለ 5 አመታት የሚቆይ 72,000 ጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ንግዶችን፤ 410800 ስራዎችን በ ገንዘብ አቅርቦት የእድገት እድላቸውንና የድጋፍ እድላቸውን በማስፋት እውን ለማድረግ በ ኦክቶበር 2022(እ/ኤ/አ) የተጀመረ ፕሮግራም ነው።

የስነልቦና ድጋፍ፡ በረጅም ጊዜ ውስጥ ከሚከሰቱ የስነልቦና ችግሮች ለማገገም በግለሰቦች ውስጥ የመቋቋም አቅምን የሚያበረታታ ዘዴ ነው።

ማገገሚያ (በግጭት ለተጎዱ)፡ የዚህ ማገገሚያ ተጠቃሚዎች በግጭት የተጎዱ ንግዶችንና ስራዎችን ለማስቀጠል በማለም የሚሰራ ነው። ተጠቃሚዎቹ የ ስነልቦና ድጋፍና የንግድ ማጎልበቻ ስልጠናዊችን እንዲሁም የማይመለስ የ ገንዘብ ድጋፍ ይደረግላቸዋል።

መቋቋም እና እድገት፡ የመቋቋም እና እድገት ተጠቃሚዎች የሚሆኑት ጥቃቅን፣አነስተኛ፣መካከለኛ እና ጀማሪ ድርጅቶች ሲሆኑ ንግዶቹ ተመልሰው ተወዳዳሪ እና የ ገንዘብ ተደራሽ እንዲሆኑ ብድር አቅርቦት እና የ ስራ ክህሎት ስልጠና ተጠቃሚ ማድረግ ነው።

ስጋት፡ የማይፈለጉ እና አሉታዊ ሁኔታዎች ወይም ውጤቶች ሲሆኑ በአጋርነት አላማዎች ስኬት ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ ውጤቶች።

ጣቢያ "የመስመር ጣቢያዎች"፡ በ መስመር ፕሮግራም ባለቤትነት የሚመራ የ ቀጥታ ግብይት መንገድ ሲሆን ለ መስመር ፕሮግራም አገልግሎት ተጠቃሚዎች የመገልገያ ድህረገፅ www.ethiomesmer.com ነው።

ተጠያሚ/ እርስዎ፡ በአጠቃላይ እርስዎን ወይም/እና ማንኛውም ሰው ወይም ተቋም በ ፕሮግራሙ ጣቢያዎች የሚጠቀሙትን ያካትታል።

 1. የ ደንብና ሁኔታዎችን ስለመቀበል
  3.1) ወደ መስመር አገልግሎቶችን ለመጠቀም ከማመልከትዎ በፊት እነዚህን ደንብ እና ሁኔታዎች በጥንቃቄ በማንበብ የመስመር ጣቢያዎች አጠቃቀምና መመሪያ አንብበው ይስማሙ።
  3.2) በደንቦችና ሁኔታዎች ላይ ካልተስማሙ እባክዎት 'cancel/ አቋርጥ' የሚለውን ይጫኑ።
  3.3) እነዚህን ደንቦች እና ሁኔታዎች እንዳነበቡ፣ እንደተረዱ እና እንደተቀበሏቸው ይቆጠራሉ
  3.4) ደንብ እና ሁኔታዎች በመስመር ከጊዜ ወደ ጊዜ በመስመር ሊሻሻሉ ወይም ሊለወጡ የሚችሉ ሲሆን። የተሻሻለውን ደንቦች እና ሁኔታዎች በተሻሻለበት ጊዜ ማግኘት ይችላሉ። ደንቦችን በየጊዜያቱ ይመልከቱ። የተሻሻሉት ደንቦች ለ እርስዎ የማይስማማ ከሆነ አገልግሎቱን ያቋርጡ። ነገር ግን አገልግሎቱን መጠቀም ከቀጠሉ፤ በተሻሻለው ውል እና ሁኔታ እንደተስማሙ እና በተሻሻሉት ደንቦች እና ሁኔታዎች እንደተስማሙ ይቆጠራል።
  3.5) የ 'እስማማለው / Agree'ን አማራጭ ከመረጡ በኋላ ማንበብዎን እና መረዳትዎን እንዲያረጋግጡ ይጠይቃሉ እና/ወይም የመስመር ፕሮግራም አገልግሎቶችን በመጠቀም ወይም መጠቀምን በመቀጠል እነዚህን ደንቦች እና ሁኔታዎች ለማክበር ተስማምተዋል።
 2. ስለ መረጃዎች እና የግላዊት መመሪያዎች

4.1) በመስመር አገልግሎት ለመጠቀም የተለያዩ እርስዎን የሚገልጹ መረጃዎችን እንደ ኢ-ሜል፣ መታወቂያ፣ ስም፣ ስልክ ቁጥር፣ የትውልድ ቀን፣ እና ሌሎች ከድርጅትዎ ጋር የተያያዙ ህጋዊ የተሞሉ ሰነዶችን መመዝገብ ይኖርብዎታል። ለ ምዝገባ ሂደት የእርስዎ የባንክ መረጃዎችን እና የተለያዩ መረጃዎችን ለማቅረብ ተስማምተዋል።

4.2) በመስመር ለሚቀርቡት አገልግሎቶች ለመጠቀም በእርስዎ የቀረብት መረጃዎች ትክክለኛ የሆኑ እና ህጋዊ ያልሆኑ ሰነዶችን መጠቀም እንደሌለብዎት ተረድተው ተስማምተዋል።

4.3) ትክክለኛውንና አስፈአጊውን የብድር መጠይቅ የ መስመር መጠይቅ ለማቅረብ ተስማምተዋል። መስመር ለተሳሳቱና ትክክለኛ ላልሆኑ ማስረጃዎች ሃላፊነት አይወስድም። የተጭበረበሩ ማስረጃዎች ኃላፊነት በተጠቃሚው ላይ ይሆናል። የሰጡንን ማስረጃ እንድንጠቀምበት፣ ለ ሦስተኛ ወገን እንድናጋራው በሚከተሉት ሁኔታዎች ላይ ብቻ ይፈቀዳል፡

ሀ) በህግ አስፈላጊ በሚሆንበት ወቅት፤

ለ) ለህግ ሂደት፣ ለፍርድ ቤት ትእዛዝ፤

ሐ) የዚህን ስምምነት ደንቦች እና ሁኔታዎች ለማስፈጸም፤

መ) የሦስተኛ ወገን መብቶችን የሚጥስ ጥያቄ ከቀረበበት፤

ሰ) ድጋፍና/ብድሩን ለማሳለጥ ለገንዘብ ተቋማት፤

 1. የብቃት መስፈርት (የመስመር አገልግሎት ለማግኘት መሰረታዊ መስፈርቶች)

5.1 በመስመር ፕሮግራም ለድጋፍ ብቁ የሚያደርጉ መስፈርቶች፡

ሀ) ኢመደበኛ ንግድ መሆን አለባቸው፤

ለ) ከ አንድ አመት በላይ በንግድ ላይ መቆየት አለባቸው፤

ሐ) ድጋፉን ንግዳቸውን ለማሳደግ እና ለማጠናከር ብቻ ለሚጠቀሙ ንግዶች።

5.2 በመስመር ፕሮግራም ለብድር ብቁ የሚያደርጉ መስፈርቶች፡

ሀ) በህግ የተመዘገቡ ንግዶች መሆን አለባቸው፤

ለ)የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸው፤

ሐ)ከ አንድ አመት በላይ በንግድ ላይ መቆየት አለባቸው፤

መ) ድጋፉን ንግዳቸውን ለማሳደግ እና ለማጠናከር ብቻ ለሚጠቀሙ ንግዶች።

5.3 ቅድሚያ የሚያገኙ፡

ሀ) በሴቶች የሚመሩ ንግዶች (በትንሹ 95%) እና በወጣቶች የሚመሩ (በትንሹ 70 %) ፤

ለ) በ ግብርና እና በ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ንግዶች።

5.4 ከ ድጋፍ እና ብድር ውጪ የሚያስደርጉ ነጥቦች፡

ሀ) ከተለያዩ ተቋማት የማይመለስ ድጋፍ ወይም ብድር የወሰዱ ንግዶች፤

ለ) የማህበራዊ ፣ የአካባቢ እና የአስተዳደር መመዘኛ መስፈርቶችን የማያሟሉ ኢንተርፕራይዞች ፤

ሐ) በመንግስት በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የተያዙ ንግዶች፤

መ) ያልተገባ ግላዊ ጥቅም የሚያስገኙ ንግዶች፣

ሰ) ከዚህ በፊት ያገኙት ድጋፍ ካለ፤

ረ) ህጋዊ ያልሆኑ እና የፖለቲካ አላማ ያላቸው ንግዶች።

6. ግጭቶችን መፍቻ መንገዶች

በዚህ ውል እና ሁኔታዎች ውስጥ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ በዚህ ስምምነት ምክንያት የሚነሱ አለመግባባቶች ወይም ልዩነቶች በሰላማዊ መንገድ ይፈታሉ።

 1. ከአቅም በላይ የሆኑ ችግሮች

መስመር በተለያዩ ከአቅም በላይ በሆኑ ችግሮች ለሚኖሩ የ መስመር ሳይት እና የአገልግሎት መቆራረጦች መዘግየቶች ምንም አይነት ሃላፊነት አይወስድም።

 1. ማስተላለፍ/ማስቀረት እና ማቋረጥን በተመለከተ

መስመር እነዚህን ህግ እና ሁኔታን ለስምምነቶች መፈጸም አለመቻል የነዚህን ህጎችና ሁኔታዎች ከተፈጻሚነት ያስቀረዋል ማለት አይደለም። የስምምነቱ ማንኛውም ድንጋጌ ሥልጣን ባለው ፍርድ ቤት ውድቅ ሆኖ ከተገኘ፣ ተዋዋይ ወገኖች በፍርድ ቤቱ አንቀጽ ላይ በተገለፀው መሠረት የተከራካሪ ወገኖችን ዓላማ ተግባራዊ ለማድረግ ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው ተስማምተዋል። ቢሆንም ሌሎች የስምምነቱ ድንጋጌዎች ከሙሉ ኃይል እና ውጤታቸው ጋር ይቆያሉ።

 1. ካሳ

እነዚህን ህጎች እና ሁኔታዎች ጋር በተያያዘ ለሚመጡ ማንኛቸውም የህግ ሂደቶች ማለትም በ መስመር ተሳታፊዎች ምክንያት ለሚመጡ በ ኃላፊዎች፣ ዳይሬክተሮች፣ ወኪሎች እና ሰራተኞች ከማንኛውም የይገባኛል ጥያቄ ላይ የጠበቃ እና የህግ ውጣ ውረድ ወጪዎች በእርስዎ የሚሸፈኑ ይሆናል።

 1. የግላዊነት ደንቦች መቀበል

የመስመርን ጣቢያ በመጠቀም ይህንን የ ግላዊነት መግለጫ መቀበላችሁን ያመለክታሉ። በግላዊ ስምምነት መግለጫ ላይ የታተቱትን ደንቦች ካልተቀበሉ፤ ከመስመር ጣቢያ ማቋረጥ አለብዎት። ይህንን የግላዊነት መግለጫ በማንኛውም ጊዜ የመቀየር መብታችን የተጠበቀ ነው።

 1. አጠቃላይ ስምምነት

እነዚህ የአገልግሎት ደንቦች የዚህን ርዕሰ ጉዳይ በተመለከተ በተዋዋይ (በተስማሚ) ወገኖች መካከል ያለውን ሙሉ ስምምነት ይመሰርታሉ።

mesmer Logo

ለዘላቂ የባንክ ተጠቃሚነት እና ዕድገት

መስመር ኢንተርፕራይዞችን የፋይናንስ፣ የንግድ ልማት እና የስነ-ልቦና አገልግሎቶችን በማቅረብ ካጋጠማቸው አደጋ ወይም ግጭት እንዲያገግሙ እና እንዲያድጉ ይደግፋል። ለማመልከት ይመዝገቡ እንዴት ማመልከት ይቻላል?


© 2024 MESMER. All rights reserved.

አበልፃጊ minab logo