mesmer logo

ስለ መስመር ፕሮግራም

የመስመር ፕሮግራም ምንድነው?

መስመር በጥቅምት 2015 የተጀመረና ለ5 አመት በመላው ኢትዮጵያ የሚተገበር ሲሆን ለ72,200 ያህል ጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ እንዲሁም ኢመደበኛና ጀማሪ ኢንተርፕራይዞች የፋይናንስ፣ የንግድ ስራ ክህሎት ስልጠና እና የስነልቦናዊ ድጋፍ አገልግሎቶችን በማቅረብ 410,800 ስራዎችን ለመደገፍ ይሰራል። በተጭማሪም ለፋይናንስ ተቋማት የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል።

መስመር በማስተርካርድ ፋውንዴሽንና እና ፈርስት ኮንሰልት ትብብር የሚተገበር በዋናነት ለሴቶችና ወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠር ላይ የሚያተኩር ፕሮግራም ሲሆን የኢፌዴሪ ስራና ክህሎት ሚኒስቴር ዋነኛ መንግስታዊ ተባባሪ አካል ነው።

01

ብድር

ለጥቃቅን አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን እንዲሁም ለንግድ ጀማሪዎች ለማሳደግ፤ስጋትን የመቋቋም አቅማቸውን ለማጎልበትና ዘላቂ የፋይናንስ ተቋማት ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ የሚያግዝ የተመቻቸ የብድር አገልግሎት

02

ድጋፍ

በግጭትና ተፈጥሮአዊ አደጋዎች በተጎዱ አካባቢዎች ለሚገኙና መደበኛ ያልሆኑ ኢንተርፕራይዞች የንግድ ስራቸውን እንዲያገግሙ የሚያግዝ ቀጥተኛ የገንዘብ ድጋፍ

03

የንግድ ልማት አገልግሎት

የኢንተርፕራይዞችን እድገት ለማረጋገጥና ከፋይናንስ ተቋማት ብድር የማግኘት አቅማቸውን ለማጎልበት ያለመ

04

ሳይኮሶሻል አገልግሎት

በስነልቦናዊ ድጋፍ አማካኝነት የኢንተርፕራይዝ ባለቤቶችን የአዕምሮ ዝግጁነት ለማሻሻልና ካጋጠሟቸው ሁኔታዎች አገግመው በድጋሚ ወደንግድ ስራቸው እንዲገቡ ለማስቻል

05

የቴክኒክ እርዳታ

የፋይናንስ ተቋማት ለኢንተርፕራይዞች የፋይናንስ ፍላጎቶች መልስ ሰጪ የሆኑ አዳዲስና አካታች አገልግሎቶችን በሚፈለገው መጠን ማቅረብ እንዲችሉ ለማገዝ

5 yrsፕሮግራም
410k+የሚፈጠር የስራ እድል
72k+enterprises

Building on this sucess, the Mastercard Foundation and First Consult present to you . . .

MESMER

. . . the Micro, Small and Medium Enterprise Recovery and Resilience Program

ማን ያስተዳደረዋል?

መስመር ፕሮግራም በሶስት እርከኖች ነው የሚተዳደረው፡ በአማካሪ ምክር ቤት፣ በብሔራዊ ኢንቨስትመንት ኮሚቴ እና በክልል የኢንቨስትመንት ኮሚቴ። 

  • አማካሪ ምክር ቤት

    ይህ የፕሮግራሙ ከፍተኛ የ አስተዳደር እርከን ሲሆን፤የስትራቴጂ አቅጣጫዎችንና መመሪያዎችን ያዘጋጃል እንዲሁም የፕሮግራሙን ከፍተኛ ተወካዮች ይይዛል።

  • ብሔራዊ የኢንቨስትመንት ኮሚቴ

    ጥቃቅን አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች መልሶ እንዲያገግሙ፣ እንዲቋቋሙ እና እንዲያድጉ የመርዳት የመጨረሻውን ዓላማ እንዲያሳካ የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት። የብሔራዊ የኢንቨስትመንት ኮሚቴ የ መስመር ፕሮግራም ትግበራን ይቆጣጠራል።

  • የክልል ኢንቨስትመንት ኮሚቴ

    በክልሎች ማመቻቸት፣መመሪያ እና አፈፃፀሙን መከታተል ይጠበቅበታል። ከአማካሪ ካውንስል በተሰጠው መመሪያ መሰረት፣ የክልል ኢንቨስትመንት ኮሚቴ እንደ አስፈላጊነቱ በሁሉም ክልሎች ሊቋቋም ይችላል።

አጋር የፋይናንስ ተቋማት

የፕሮግራሙ የብድር ፈንድ በአጋር የፋይናንስ ተቋማት አማካኝነት የተቀመጡትን መስፈርቶች አሟልተው ወደሚመረጡ ኢንተርፕራይዞች የሚደርስ ይሆናል። በፈርስት ኮንሰልት አስተባባሪነት አጋር ባንኮች የቅርንጫፍ ተደረሽነታቸውን በመጠቀም ኢንተርፕራይዞች ለፕሮግራሙ እንዲያመለክቱ ያግዛሉ እንዲሁም ለተመረጡ ኢንተርፕራይዞች የብድር ሂደቱን ያካሂዳሉ። ባንኮቹ ከማይክሮፋይናንስ ተቋማት ጋር አጋርነት በመፍጠር በገጠር አካባቢዎች የሚገኙ ኢንተርፕራይዞችን እንዲደርሱ ይጠበቃል።

ባለድርሻ አካላት

ይህ መርሃ ግብር ሂደቱን በማቀላጠፍ ረገድ ልዩ ሚና ባላቸው ሶስት ባለድርሻ አካላት የሚተገበር ነው።

mesmer Logo

ለዘላቂ የባንክ ተጠቃሚነት እና ዕድገት

መስመር ኢንተርፕራይዞችን የፋይናንስ፣ የንግድ ልማት እና የስነ-ልቦና አገልግሎቶችን በማቅረብ ካጋጠማቸው አደጋ ወይም ግጭት እንዲያገግሙ እና እንዲያድጉ ይደግፋል። ለማመልከት ይመዝገቡ እንዴት ማመልከት ይቻላል?


© 2024 MESMER. All rights reserved.

አበልፃጊ minab logo